“የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከአሸባሪው ትህነግ ዘረፋ በተረፈው ንብረት እንኳን መስራት እንዳይችል ሆኖ ወድሟል” የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው

189

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ላይ ከፈጸመው ዝርፊያ በተጨማሪ በቀረው ንብረቱ እንኳን ስራ እንዳይጀምር አድርጎ እንዳወደመው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ ውድመትና ዝርፊያ ያደረሰበትን የወልድያ ዩኒቨርሲቲን ተመልክተዋል።
የሽብር ቡድኑ የዘረፈውን የዩኒቨርሲቲውን ንብረት ጭኖ ሲወስድ መውሰድ ያልቻለውን አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርጎ አውድሞታል።
ይህን የተመለከቱት ሚኒስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው የዩኒቨርሲቲው ውድመት የሽብር ቡድኑ አባላት መንግስትን ወይንም ፖለቲከኞችን ሳይሆን ሕዝብን አምርረው የሚጠሉ፤ ሕዝብና የሕዝብ የሆነን ሁሉ ከማጥፋት የማይመለሱ መሆናቸውን ያሳየ ነው ብለዋል።

በዚህ ደረጃ በሕዝብ ላይ የከፋ ጥላቻ ከተጠናወተው የሽብር ቡድኑ ተግባር ለቀጣይ ትምህርት መውሰድ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲውም ከቀደመው በተሻለ ሁኔታ መልሶ ይገነባል ብለዋል።
የሰሜን፣ የደቡብ ወሎ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስም የሽብር ቡድኑ ተግባር ምንም ግብ የሌለው ነው ብለዋል። ብጹዕነታቸው ይህንን ውድመትና ጥፋት አዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መጥተው በዓይናቸው ቢመለከቱ ሚዛናዊ ፍርድ መስጠት ያስችላል ነው ያሉት።
“የትግራይ እናት ላከችን” ያለው የጥፋት ኀይል የፈጸመው እኩይ ድርጊት አሳዛኝ ነው ሲሉም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ያለፉት ወራት አሸባሪው ትህነግ ካደረሰብን ጉዳት በላይ እስላም ክርስቲያኑ በአንድነት የቆምንበት፣ ለቀጣይም ትምህርት ያገኘንባቸው ነበሩ ያሉት ደግሞ የወልድያ ከተማ የሠላም ኮሚቴ አባል ሃጂ ያሲን እድሪስ ናቸው።
ሃጂ ያሲን የሽብር ቡድኑን ወራሪዎች የፈጸሙት ክፋት፣ ዝርፊያና ውድመት ከሰው ልጅ የማይጠበቅ ነው ብለውታል።
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

Previous articleአሸባሪው ትህነግ በቆቦ ከተማ በአንድ ቀን 89 ንጹሃንን ገድሎ በጅምላ መቅበሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next articleፋኖ ዘነቡ መንግሥቴን በጨረፍታ…