
በቂ የደኅንነት ጥበቃ እንደሚደረግላቸውም አስታውቋል።
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ያደረጉትን ጥሪ ምክንያት በማድረግ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ከኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገሮች የሚመጡ እንግዶች በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ሁሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መንቀሳቀስ እንዲችሉ በቂ የደኅንነት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል፡፡
ይህ የተገለጸው በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሀገር መከላከያ ሰራዊቱ፣ ከሪፐብሊካን ጋርድ፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት የተውጣጣው ጥምር የጸጥታ ኃይል ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታን በገመገመበትና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ባስቀመጠበት መድረክ ላይ ነው፡፡
በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ከኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገሮች የሚመጡ እንግዶች ወደ ሀገር ቤት በሚመጡበት ጊዜ ያለምንም የሰላምና የጸጥታ ስጋት በፕሮግራማቸው መሰረት መንቀሳቀስ እንደሚችሉና ያለው የጸጥታ ሁኔታም አስተማማኝ መሆኑን ጥምር የጸጥታ ኃይሉ አስታውቋል፡፡
ጥምር የጸጥታ ኃይሉ አጠቃላይ ያለውን ሀገራዊ የጸጥታ ሁኔታን ገምግሞ በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስምሪት መግባቱንም አረጋግጧል፡፡
መረጃው የፌዴራል ፖሊስ ነው
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
