በሀገራዊ ጥሪው ወደ ሀገር የሚገቡ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጉን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

160

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡

ወደ ሀገር ቤት የሚመጡ እንግዶችን በባሕር ዳር ከተማ ለማስተናገድ ዝግጅት መደረጉን የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) ተናግረዋል።

ዶክተር ድረስ የባሕርዳር ከተማ ብዙ ገፀ-በረከት ያላት በመሆኗ በርካታ የቱሪስት እና የኢንቨስትመንት ፍሰቶችን እያስተናገደች የምትገኝ ውብ፣ ምቹ እና ጽዱ ከተማ ናት ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በንጹሐን ሕይወት፣ ሀብት እና ንብረት ላይ ጥፋት እያደረሰ ቢሆንም በሕዝቡ የተባበረ ክንድ እና በጀግናው ጥምር ጦር እየተደመሰሰ በሚገኝበት ወቅት ላይ ዲያስፖራው ወደ ሀገር ቤት መጠራቱ ለድሉ ስኬታማነት ጉልህ ድርሻ ያለው መሆኑን ዶክተር ድረስ ገልጸዋል።

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ከባለሀብቱ፣ ከአስጎብኝ ማኅበራት እና ከፀጥታ ኀይሉ ጋር በመቀናጀት የእንግዶችን ምቾት ለመጠበቅ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ያጠናቀቁ መሆኑንም አመላክተዋል።

ከንቲባ ዶክተር ድረስ ከተማዋ ከታኅሣሥ 25/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለእንግዶቿ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ የተዘጋጀች መሆኑንም ተናግረዋል። ከጥር 01/2014 ዓ.ም እስከ ጥር 05/2014 ዓ.ም ድረስ እንግዶች በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የልማት አማራጮችን የያዙ የአውደ ጥናት መርኃ ግብሮችን በማከናወን ዲያስፖራው ያለውን ሀብትም ሆነ እውቀት በከተማዋ እንዲያውል የሚያስችሉ ልዩ ልዩ አማራጮች እንደሚቀርቡ መግለጻቸውን ከባሕር ዳር ከተማ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና አስተሳሰቡ በኢትዮጵያ ምድር ዳግም ላይነሱ መቀበር እንዳለባቸው የደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ፡፡
Next article“በአማራ ክልል ሕገወጥ ተኩስ በሚፈጽሙ ሰዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል” የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ