“የሀገር ኅልውናን ለማስቀጠል ግንባር ድረስ በመዝመት ደማቅ የታሪክ ዐሻራ እያሳረፍን በመኾናችን ደስተኞች ነን” ዘማች የሕክምና ባለሙያዎች

85

ታኅሣሥ14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በየትኛውም የውጭም ኾነ የሀገር ውስጥ ጠላት ተደፍራ የማታውቅ ኢትዮጵያ፤ ጀግኖች ልጆቿ ከምንም በላይ ነጻነታቸውን አጥብቀው የሚፈልጉ ለዚኽም የሚከፈለውን ዋጋ ኹሉ በአንድነት የሚከፍሉ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን ጀግንነት፣ ጥልቅ የሀገር ፍቅር፣ ሀገር ስትደፈር ሆ! ብሎ መነሳት ከዛም ጠላትን ድባቅ መምታት መገለጫቸው ነው፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚፈልጉ የውጭ ሀገር ጠላቶች ጋር አብሮ የፈጸመውን ክህደት ለመቀልበስ ኢትዮጵያውያን በየሙያቸው ዘምተዋል፡፡
ለዓመታት ሀገር ከመከፋፈል፣ ከመዝረፍ፣ ከማጭበርበር እና ሕዝብን ከሕዝብ ማጋጨት ግብሩ የሆነው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን አኹን ከኢትዮጵያ ምድር ሊነቀል ጫፍ ደርሷል፡፡ በመኾኑም ኹሉም ፊቱን ወደ ግንባር በመመለስ ሀገሩን ለማዳን ቀን ከሌሊት እየሠራ ይገኛል፡፡ በኅልውና ዘመቻው አበርክቷቸውን እየተወጡ ከሚገኙት መካከል የሕክምና ባለሙያዎች ይገኙበታል።
“የሀገር ኅልውናን ለማስቀጠል ግንባር ድረስ በመዝመት ደማቅ የታሪክ ዐሻራ እያሳረፍን በመኾናችን ደስተኞች ነን” ብለዋል ዘማች የሕክምና ባለሙያዎች።
ከጎንደር ከተማ አስተዳደር በግንባር ተገኝተው ለሠራዊቱ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጡ ያገኘናቸው ሲስተር ጽጌረዳ አድማሱ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመመከት የኹሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመኾኑ ግንባር ድረስ መገኘታቸውን ነግረውናል፡፡
“የኅልውና ዘመቻው የሁላችንም ነው፤ ምክንያቱም ቡድኑ የኹሉም ጠላት ነው” ብለዋል የሕክምና ባለሙያዋ፡፡
ሀገር የወታደር ብቻ አይደለችም፤ በኹሉም የሙያ ዘርፍ ያለ ኹሉ የሀገር ነቀርሳ የኾነውን ቡድን ከምድራችን እስኪነቀል ከፀጥታ ኀይሉ ጋር ግንባር ድረስ ጭምር በመዝመት የታፈረች እና ሉዓላዊነቷ የተከበረ ሀገሩን ለትውልዱ ማስረከብ እንዳለበት ተናግራለች።
ባለሙያዋ እንዳለችው የሠራዊቱ ጀግንነት፣ የሀገር ፍቅር፣ ጠላትን እየደመሰሰ የሚያስመዘግበው ድል የሕክምና ባለሙያዎችን እጅግ እንደሚያስደስት እና የዚህ ድል አካል በመሆናቸው ኩራት ይሰማቸዋል፡፡ አረመኔው ቡድን ለሕጻናት፣ ለሴቶች፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች እንዲኹም ዓለም በቃኝ ብለው በሃይማኖት ተቋማት ቀሪ ሕይወታቸውን እያሳለፉ ላሉ እንኳን የማይራራ አረመኔ ቡድን በመሆኑ እስከመጨረሻው #መቀበር አለበት ብላለች፡፡ ለዚኽም ኹሉም መረባረብ እንዳለበት ነው መልዕክት ያስተላለፈችው፡፡
ሌላኛዋ ዘማች የሕክምና ባለሙያ ሲስተር ራሔል መልካሙ ሀገር የኹሉም በመኾኗ ኹሉም የሚጠበቅበትን ኀላፊነት መወጣት አለበት ብላለች፡፡ መዝመት እና ጠላትን መፋለም የወታደር ብቻ አለመኾኑን በመረዳት ኹሉም በሙያው የሀገር ጠላት የኾነውን ቡድን #ለማጥፋት በሚደረገው ዘመቻ ሊሳተፍ እንደሚገባም ገልጻለች፡፡
ከሀገር በላይ የሚበልጥ ነገር የለም ያለችው ሲስተር ቢታኒያ ምሥጉን በግንባር ተገኝታ በሙያዋ ማገልገሏ ትልቅ ክብር ተሰምቶኛል ነው ያለችው፡፡
ያለ መስዋእትነት ነጻነት እንደማይገኝ የገለጸችው የሕክምና ባለሙያዋ የሀገር ነቀርሳ የሆነውን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን ለመቅበር በሚደረገው ርብርብ እስከ መጨረሻው እንደምታገለግል ተናግራለች፡፡
የኅልውና ዘመቻው ኹሉንም ኢትዮጵያዊ የሚመለከት በመኾኑ ይህንን የታሪክ አጋጣሚ በመጠቀም ጣረ ሞት ላይ ያለውን ወራሪ ቡድን #ለመቅበር ኹሉም ሊሳተፍ ይገባልም ብላለች፡፡
ዘጋቢ፡-የማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous article“ከኅልውና ዘመቻው ዓላማ አንፃር ጦርነቱ አልተቋጨም፤ በዘመቻው አኩሪ ገድል ለፈጸሙ የወገን ጦር አባላት የክልሉ መንግሥት ክብር አለው” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
Next articleአብዛኛው አካባቢዎች ከሽብር ቡድኑ ነጻ መሆናቸውን ተከትሎ የአማራ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡