
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃለፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የክልሉ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ ማሻሻያ አድርጓል፡፡ ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ጠዋት 12 ሰዓት የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ በመምጣቱ የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎች እንዳይዳከሙና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዲያስፖራዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ማሻሻያ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
በዚህም መሰረት የሰዓት እላፊ ገደቡ ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋት 11 ሰዓት ድረስ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
