
ታኅሣሥ 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዳያስፖራዎች በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የሚያደርጉበት የአገልግሎት መስጫ ክፍል በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ማዘጋጀቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ገለጹ።
ዶክተር ኢዮብ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ የአገልግሎት መስጫ ክፍሉ እንዲከፈት የተደረገው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት ለተጎዱ ወገኖች በቀላሉ ድጋፍ ማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ መመቻቸት አለበት በሚል በተደጋጋሚ ጊዜ የቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ነው ብለዋል።

ዳያስፖራዎች ወደ አገልግሎት መስጫ ክፍሉ በመሄድ በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ በተከፈተው የንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥር 1000439142786 ገንዘብ ማስገባት እንደሚችሉ ተገልጿል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
