
ታኅሣሥ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አንድ ሚሊዮን ዳያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ጥሪ ማስተላለፋቸው ይታወሳል። ወደ ሀገር ቤት የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለማስተናገድ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሟል።
በብሔራዊ ኮሚቴው የሥራ እንቅስቃሴ ዙሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መረጃ ያጋሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን “ብሔራዊ ኮሚቴው የ’ታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት’ መርኃግብርን ለማስተናገድ ዝግጅቱን አጠናቋል” ብለዋል።

በሀገራዊ ጥሪው አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ላሳዩ በሙሉ የሰጡትን ታላቅ ምላሽ እናደንቃለን ነው ያሉት አቶ ደመቀ።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
