አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ውድመት እና ዝርፊያ ማድርሱን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።

147

ወልድያ፡ ታኅሣሥ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ ውድመት እና ዝርፊያ ማድርሱን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋሁን ባታብል ገልጸዋል። አሸባሪ ቡድኑ በዞኑ መጠነ ሰፊ ውድመት አድርሷል፤ በርካታ ሰው ገድሏል፤ አቁስሏል፤ መስዋእትነትም ተከፍሏል ነው ያሉት። ወራሪ ቡድኑ ሴቶችን ደፍሯል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ረጅም ጊዜያትን በወረራ በመያዙ በሰብዓዊ እና ቁሳዊ ንብረቶች ላይ ከባድ ኪሳራ ማድርሱንም ተናግረዋል።

ወራሪ ቡድኑ በጤና፣ በትምህርትና በፀጥታ ተቋማት ከፍተኛ ውድመት እና ዘረፋ ፈጽሟል፤ያልቻለውን ደግሞ ጥቅም እንዳይሰጥ አድርጓል ነው ያሉት። የትምህርት ቤት ወንበሮችን እየፈለጠ ለማገዶ ተጠቅሟል፤ ትምህርት ቤቶች ላይ አስክሬን በመቅበር የክፋት ጥጉን አሳይቷል ብለዋል።

አስተዳዳሪው “ወራሪ ቡድኑ በተቋማት ላይ ከፍተኛ ዝርፊያ ቢፈጽምም ድንጋይ ላይ ተቀምጠንም አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተናል” ብለዋል።

የደረሰው ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ከባድ ቢሆንም ጉዳቱ አማራን የበለጠ አንድ ያደረገ ነው፤ አመራሩ እና ኅብረተሰቡ ተሳስቦ ለመሥራት ምክክር ማድረጋቸውንም ነው ያስረዱት።

በአሁኑ ወቅት የወረዳው ሕዝብም እየተረጋጋ ነው፡፡ ስምሪትም ተሰጥቷል፤ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችም አካባቢው ወደ ተረጋጋ እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን ተረድተው ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው-ከወልድያ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleየባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ማረሚያ ቤት መምሪያ ለወገን ጦር ድጋፍ 580 ሺህ ብር ማሰባሰቡን ገለጸ፡፡
Next article“ብሔራዊ ምክር ቤቱ የ’ታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት’ መርኃግብርን ለማስተናገድ ዝግጅቱን አጠናቋል” አቶ ደመቀ መኮንን