የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

232

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሽንፈትን ተከናንቧል፣ የተረፉ አባላቱም ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነዋል ብለዋል። ይሁን እንጅ የሽብር ቡድኑ መሪዎች ጦርነቱን ለሰላም ብለው እንዳፈገፈጉ አድርገው ውሸት በመንዛት የትግራይን ሕዝብ እንዲሁም የዓለምን ማኅበረሰብ እያታለሉት ነው ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው ።
ባለፉት ጊዜያት ሐሰተኛ ዜናዎችን በማሰራጨት የሽብር ቡድኑን ሲያግዙ የነበሩ ሲ ኤን ኤንና የመሳሰሉ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኀኖች ዛሬም የሽብር ቡድኑን ሽንፈት ስልታዊ ማፈግፈግ እያሉት እንደሚገኙ በመግለጫው ተነስቷል።
በአሁኑ ሰዓት የሽብር ቡድኑ ከአማራና ከአፋር ክልሎች በአብዛኛው በሚባል ደረጃ ተጠራርጎ እንደወጣም በመግለጫው ተነስቷል።
በኢትዮጵያ ላይ ፍትሐዊነት የጎደለው ጫና እያደረጉ ያሉ ዓለምአቀፍ ተቋማትን አስመልክቶም በመግለጫው ተብራርቷል። የሽብር ቡድኑ የተባበሩት መንግስታት የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ለእኩይ ዓላማው ማስፈጸሚያ እንደ መሳርያ እየተጠቀመ ይገኛል ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በማይመለከተው ጉዳይ ሁሉ ሳይቀር ከ12 ጊዜ በላይ በኢትዮጵያ ላይ የመከረው ተቋሙ ከሁለት ቀናት በፊት ያደረገው ስብሰባ በኢትዮጵያ ወዳጅ በሆኑ ሀገራት ያለ ውጤት ተበትኗል ተብሏል።
የተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትም በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እየፈጠረ ይገኛል ነው ያሉት። ከዚህ በፊት ምርመራ አድርጎ የነበረው ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በድጋሜ ሊያደርግ ያሰበው ምርመራ በኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለውም ሚኒስትር ዴኤታው በመግለጫው ተናግረዋል።
ሌላው በመግለጫው የተነሳው ሀገራዊ ምክክርን በተመለከተ ነው። መንግስት ዋናዋና ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ምክክር ያስፈልጋል የሚል እምነት አለው ብለዋል። ይህንንም ለማድረግ ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሆነና አስተባባሪ ኮሚሽን እንዲቋቋም ለምክርቤቱ አባላት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት እንደሚገኝ ተመላክቷል።
ይሁን እንጅ ይህንን ጉዳይ ከሽብር ቡድኑ ጋር መንግስት ድርድር ሊያደርግ ነው በሚል የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ፤ ይሄ በፍጹም ስህተት ነው ብለዋል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታው።
በፈረደ ሽታ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleበተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።
Next articleወደ ሀገር ቤት ለሚመጡ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች የኢንቨስትመንት አማራጮች መዘጋጀቱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ።