በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።

122

ታኅሣሥ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም በሀገሪቱ ጦርነት እንዳይከሰት የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ብዙ መልፋታቸውን አስታውሰዋል፡፡ በጦርነቱም የሰው ልጅ ህይወት ጠፍቷል፤ ብዙዎቹም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡
የሃይማኖት ተቋማት እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መውደማቸውንም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
ለተፈናቀሉ ወገኖች ኢትዮጵያውያን የቻሉትን ድጋፍ ማድረጋቸውን በመጥቀስ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አሁን ሀገር እያስመዘገበችው ያለውን ድል በመጥቀስም ይህ ድል በተገኘባቸው አካባቢዎች ሁሉ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ስለሚመለሱ ዘላቂ መቋቋሚያ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኮሚቴ አቋቁሞ የጉዳቱን መጠን የመለየት ሥራ እየሠራ መሆኑን የጠቆሙት ተቀዳሚ ሙፍቲ የባንክ ሂሳብ የተከፈተ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ድጋፉ በአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም ከወለጋ አካባቢ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል መሆኑን ፋብኮ ዘግቧል፡፡
የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች የሰላምን መንገድ እንዲያሳዩ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ በመግለጫቸው አሳስበዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous article“የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና ሕዝብ ለአማራ ሕዝብ ያደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያዊነት ነጸብራቅ ነው” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
Next articleየመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።