“በአሸባሪ ቡድኑ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋምና የደረሰውን የሀብት ወድመት መልሶ ለመተካት ሁሉም ይዘጋጅ” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

97

ታኅሣሥ 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በወቅታዊ ጉዳይ መልዕክት አስተላልፈዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “የትግል አቅጣጫ” ያሏቸውን ጉዳዮች አመላክተዋል።
“አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ያደረሰብን ጥቃት መቸውም የሚረሳ አይደለም። በተባበረ ክንዳችን እየደመሰስነው እንገኛለን። ጠላት ግን መጥፋቱን ወይም ስጋት መሆን ከማይችልበት ደረጃ መድረሱ ገና አልተረጋገጠም። በመሆኑም አሁን ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ጊዜያትም የሁላችን ዝግጁነት ይጠይቃል” ብለዋል።
በአሸባሪ ቡድኑ የደረሰውን የሀብት ወድመት መልሶ ለመተካትና የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም ሁሉም እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በሚቻለው መንገድ ሁሉ ፈጥኖ ርብርብ ካልተደረገ ከጦርነቱ በላይ የአማራ ሕዝብ ለተራዘመ ጊዜ እንደሚጎዳ ማወቅ ይገባል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የተጀመረውን የመስኖ ልማት ማጠናከር፣ የከተሞችን የንግድ እንቅስቃሴና የመሠረተ ልማት ሥራዎች በማፋጠን የሥራ እድል መፍጠር እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
“በቀጣይ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመውሰድ የተቀዛቀዙ ከተሞችን ማነቃቃት፣ ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት እና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ልዩ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል፤ ለዚህ ደግሞ የተረጋጋ አካባቢና ማኅበራዊ ህይወት ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ ሁሉም ከመንግሥት ጎን ይሰለፍ” ነው ያሉት።
የአካባቢን ሰላምና ደኅንነት በማረጋገጥና የትግል አቅጣጫን በመቃኘት ከደረሰው ጥፋት ፈጥኖ በመቋቋም ለክልሉ ኅብረተሰብ የህይወት መሻሻል ብሩህ ተስፋን እናሳያለን ብለዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous article“ሁሉም ለቀጣይ ትግል መዘጋጀት ባለበት ወቅት ጥይትን ያለ አግባብ ማባከን ኀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
Next articleሕዝብን ከረሃብ እልቂት የታደገው የብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ አዋጅ በወልድያ ከተማ!