‹‹መንገድ ሲመሩ የነበሩ የውስጥ ባንዳዎችን ወደ ሕግ ማቅረብ ተጀምሯል››

478

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአሸባሪው ትህነግ እና ኦነግ ሸኔ ሸዋሮቢትን ከተማ እንዲወሩና እንዲያወድሙ መንገድ ሲመሩ የነበሩ፣ መረጃ በመስጠት የተባበሩና በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ የውስጥ ባንዳዎችን በመለየት ወደ ህግ ማቅረብ መጀመሩን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዘነበ ተክሌ እንደገለሻጹት፤ የአሸባሪው ትህነግ ወራሪዎች ሸዋሮቢት ከተማ በገቡበት ወቅት ሁሉንም የግለሰብ ቤቶች አንኳኩተው ዘርፋ ማካሄዳቸውን፣ አዛውንቶች፣ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ታዳጊዎች እና እናቶችን መድፈራቸውን ጠቁመው፤ በርካቶች ለከፋ የጤና እክል ተዳርገዋል ብለዋል።
ምክትል ከንቲባው እንደተናገሩት የአሸባሪው ትህነግ ወራሪዎች ሸዋሮቢት ከተማን በወረሩበት ወቅት ሁሉንም የግለሰብ ቤት አንኳኩተው ዘርፋ የፈፀሙ ሲሆን ተቋማትን ዘርፈዋል፤ የተቀረውን ደግሞ ሆን ብለው አውድመዋል። የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ አባላት እና ቡድንም ከአሸባሪው ትህነግ ጋር በመተባበር አስከፊ ተግባር ሲያከናውን እንደነበርም አረጋግጠዋል።
አሸባሪዎቹ ነዋሪዎችን ገድለዋል፣ ንብረት ዘርፈዋል፤ አውድመዋል፤ ሴቶችን አስገድደው ደፍረዋል፣ የንግድ ተቋማትን አውድመዋል ነው ያሉት። ዘገባው የኢፕድ ነው
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

Previous article‹‹እየተገኘ ያለው ድል ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን ወደፊትም አንድ ሆነው በአሸናፊነት መቀልበስ እንደሚችሉ ሕያው ማሳያ ነው›› ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶክተር)
Next article”ጥልቅ ጉድጓድ ከሞት ላያስጥላቸው፣ መቆፈሩ ተረፋቸው”