‹‹በአሸባሪው የወደሙ መሠረተ ልማቶችን የመገንባትና የተፈናቀሉትን የማቋቋም ኃላፊነት የሁላችንም ነው›› አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

93

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራና በአፋር ክልሎች የወደሙ መሠረተ ልማቶችን የመገንባትና የተፈናቀሉ ወገኖቻችን መልሶ የማቋቋም ኃላፊነት የሁላችንም መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡
ለክልሎቹ ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ሐብት እያሰባሰብን እንገኛለን ያሉት
አቶ ደስታ ሌዳሞ በአሸባሪው ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው የአማራና የአፋር ክልሎችን መልሶ ለማቋቋም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ነው ብለዋል።
እንደ ሀገር የተጋረጠውን ፈተና ለማለፍ ሁሉም አቅሙን አሟጦ መተባበር ይኖርበታል ብለዋል።
ተፈናቃዮችን የማቋቋሙ ኃላፊነት ሁሉንም ክልል ይመለከታል ያሉት አቶ ደስታ፤ የሲዳማ ክልልም ከዚህ ቀደም አጋርነቱን ለማሳየት በባሕር ዳርና ሰመራ ከተሞች በመገኘት የገንዘብ እንዲሁም የአይነት ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።
አሁንም ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ሐብት እየሰባሰብን እንገኛለን። በቅርቡ በአማራ ክልል ተገኝተን ተጨማሪ የማቋቋሚያ ድጋፍ እናደርጋለን ነው ያሉት፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳስታወቁት፤ አሸባሪው ትህነግ በወረራ በቆየባቸው የአማራና የአፋር ክልሎች በሰው ልጆች ላይ ሊደረግ የማይገባው እጅግ ዘግናኝ ግፍ ፈጽሟል። በንብረት ላይም እጅግ አሳዛኝ ውድመትና ዘረፋ ተፈጽሟል። ዘገባው የኢፕድ ነው
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

Previous article“ኢትዮጵያን የምትፈራና የማትደፈር ሀገር ለማድረግ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን መቀላቀል ይገባችኋል” አቶ ላቀ አያሌው
Next articleበሦስተኛው የቱርክ አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን ቱርክና ኢትዮጵያ ትብብራቸውን ማጠናከር የሚያስችሉ ስኬታማ ምክክሮች መካሄዳቸውን መንግሥት አስታወቀ፡፡