
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የገቢዎች ሚኒስትር እና ተጠሪ ተቋማት ለደቡብ ወሎ ዞን ትናንት ድጋፍ ሲያደርጉ የገቢዎች ሚኒስትሩ ላቀ አያሌው እንደገለጹት የትግራይ ወራሪ ቡድን አንሶ ለማሳነስ፣ ወርዶ ለማውረድ እና ጠቦ ለማጥበብ ያደረገው ጥረት ሁሉ በወገን ጦር ጠንካራ ምት አልተሳካለትም፡፡
ወራሪ ቡድኑ በአማራ እና አፋር ክልሎች ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች ሰው የሆነ ፍጡር ሁሉ የማይፈጽመውን አስነዋሪ ድርጊት ፈጽሟል ነው ያሉት፡፡ ወራሪውን ቡድን የሀገር ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ ለማድረስም የጋራ ትብብር እና ጥረት እንደሚጠይቅ አቶ ላቀ አሳስበዋል፡፡
ዘራፊው ቡድን በስልጣን ዘመኑ ሕዝቡን በመዋቅር ቢከፋፍልም የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገር ጉዳይ አንድ በመሆኑ ዛሬም እንደትናንቱ በተባበረ ክንድ ከጸጥታ ኀይሉ ጎን በመሰለፍ በርካታ ድሎች እንደተገኙ ተናግረዋል፡፡
አቶ ላቀ እንደ አማራ እና እንደ ኢትዮጵያ አንድ መሆን ያስፈልጋል፤ አንድ እንዳንሆን የሚከፋፍለውን አካልም ከሽብር ቡድኑ ለይተን ማየት የለብንም ነው ያሉት።
ሚኒስትሩ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ለወጣቶ ባስተላለፉት መልዕክት የውስጥ ባንዳን እና የውጭ ጠላት ሲመጣ ሀገርን መታደግ የሚችለው ጠንካራ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሲገነባ በመሆኑ ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን መቀላቀል አለባችሁ፤ ይህ ሲሆን ጠንካራና የማትደፈር ሀገር መፍጠር ይቻላል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው -ከደሴ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
