
አዲስ አበባ፡ ታኅሣሥ 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሴቶችና ህጻናት የደረሰውን ገፍ ለዓለማ አቀፍ ማኅበረሰብ ለማስገንዘብና የውጭ ጫናን የሚቃወም የበቃ # NoMore ሰልፍ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ሰልፈኞቹ አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአማራና በአፋር ክልሎች የፈፀማቸውን ጾታዊ ጥቃቶች በመልዕክቶቻቸው ከማስተጋባት ባለፈ የውጭ ጫናን በቃ በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
በሰልፉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኢፌዴራል ተቋማት የተውጣጡ የሥራ ኅላፊዎችን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው የከተማዋ ሴቶች ተሳትፈዋል።
በሀገሪቱ ሁሉም ክልሎች እና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለተፈናቀሉ ዜጎች እና ለጸጥታ ኅይሉ ድጋፍ የሚውል ሁለት ቢሊዮን ብር ማሰባሰብ እንደተቻለም የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒትሯ ኤርጎጌ ተስፋየ (ዶክተር) ተናግረዋል።
በሰልፉ እየተሳተፉ የሚገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሸባሪው ትህነግ በሴቶችና ህፃናት ላይ ያደረሰው ግፍ ታሪክ ይቅር የማይለው ነው ብለዋል።
የሽብር ቡድኑ እያደረሰ ያለውን አሰቃቂ ግፍ በፅናት በመቀልበስ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ማረጋገጥ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ:–ድልነሳ መንግሥቴ–ከአዲስ አበባ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
