‹‹የምክር ቤቱ ውሳኔ ለኢትዮጵያ ትርጉም የለሽ ነው›› አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

229

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ በኢትዮጵያ ላይ ምንም አይነት ትርጉም የሌለውና ኢትዮጵያ የማትቀበለው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ፡፡
አምባሳደር ዲና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ አንድን ሉዓላዊት ሀገር በመግፋትና በማስጨነቅ ለአገዛዝና ለበላይነታቸው እንዲመች የማድረግ አባዜ ነው፡፡ በመሆኑም ውሳኔው ኢትዮጵያ የማትቀበለውና ምንም አይነት ትርጉም የሌለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ ምርመራ አድርገው የምርመራ ውጤቱን ይፋ አድርገዋል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ኢትዮጵያም የማትስማማባቸው ነገሮች ቢኖሩም በሂደቱ ግን እንደምትስማማ ገልጻ የቀረቡትን የመፍትሄ ሐሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት ላይ እያለች የተጠራ ስብሰባ ነው፡፡ ውሳኔውም ሀገሪቱ ላይ አላስፈላጊ ጫናና ወከባ ለመፍጠር ያለመ እንጂ ሌላ የሚፈይደው ነገር የለም ብለዋል፡፡
የጥምር ቡድኑ ያደረገውን ማጣራት ወደጎን ብለው ሌላ አጣሪ ቡድን ለማቋቋም መፈለጋቸው እነሱ ያልጀመሩትና ያልፈጸሙት ነገር ተቀባይነት እንደማይኖረው ለማሳየት ያደረጉት ጥረት መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም የስውር ቅኝ አገዛዝ ለማድረግና ጫና ለመፍጠር ነው ብለዋል።
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኘው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
Next articleየሽብር ቡድኑ በአማራ እና አፋር ክልሎች በሴቶች እና ህጻናት ላይ የፈጸመውን ጾታዊ ጥቃት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚያስገነዝብ ሰልፍ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡