ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኘው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

322

ታኅሣሥ 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በወገን ጦር በተገኘው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ያስተላለፉት መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል።
በወራሪው የጠላት ኃይል ቁጥጥር ስር የነበሩ አከባቢዎችን ነፃ የማውጣት እርምጃን ተከትሎ የወልዲያ ከተማ እና አካባቢው መንግሥት በወሰደው ጠንካራ የማጥቃት እርምጃ ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣት በመቻሉ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን አብሮ ደስ አለን።
ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ እና አፋር ክልል ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ላደረጋችሁት ብርቱ ርብርብ እና አኩሪ ተጋድሎ ከልብ እናመሰግናችኋለን፤ እናከብራችኋለን።
ለዚህ ታሪካዊ የድል ምዕራፍ ስላበቃችሁን ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ።
አሁንም የድል ግለቱን ጠብቆ በወራሪው የጠላት ኃይል ቁጥጥር ስር ያሉ ቀሪ ጥቂት አካባቢዎችን በአጭር ጊዜ ነፃ የማውጣት እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ሀገራችን ኢትዮጵያን ከገጠማት ፈተና እንዳትላቀቅ ብሎም የከፋ ጫና ውስጥ እንድትወድቅ ከውስጥ እና ከውጭ ያሉ ኃይሎች ተባብረው እየሰሩ መሆናቸው በግልፅ ይታወቃል።
እነዚህ ለጥፋት ያበሩ ኃይሎች የኢትዮጵያን ውድቀት ለማብሰር ሁሉንም ምድራዊ የጥፋት እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ እንደማይሉ በገሃድ በሚፈፅሙት ጫና እና ሴራ መረዳት ይቻላል።
ይሁንና ኢትዮጵያዊነት የነሱን የጥፋት ድግስ ታግሶ ለማስተናገድ የሚፈቅድ የሞራል ስብራት እንደሌለው በየጊዜው የሚያስመዘግባቸው አኩሪ ድሎች በቂ ማሳያ ናቸው።
በዚህ አጋጣሚ በተለያዩ ክፍለ አለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በ”No More” ዓለም አቀፍ ንቅናቄ በተሰለፋችሁበት መድረኮች ለምታደርጉት ተጋድሎ ከልብ እናመሰግናለን።
የውጪውን ግንባር በደማቅ ኢትዮጵያዊ አንድነት እና ህብረት ለምታደርጉት ሁሉአቀፍ ርብርብ እና ትርጉም አዘል ጫና ልዩ አክብሮታችን እና አድናቆታችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ።
ሁሉም ለጥፋት ግንባር ፈጥረው ይባክናሉ፤ ይሁንና በጠንካራ የአንድነት መንፈስ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ዳር እስከዳር አኩሪ ድሎች እያስመዘገብን ወደፊት መጓዛችንን እንቀጥላለን።
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous article❝እንኳን ደስ አለን! ድሉ የመላ ኢትዮጵያውያን ድል ነው❞ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
Next article‹‹የምክር ቤቱ ውሳኔ ለኢትዮጵያ ትርጉም የለሽ ነው›› አምባሳደር ዲና ሙፍቲ