
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በ2013 /2014 የምርት ዘመን በዘር ከተሸፈነው መሬት ውስጥ 76 በመቶ ያህሉ መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ አምሳሉ ጎባው ለምርቱ በወቅቱ መሰብሰብ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እና የልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አቶ አምሳሉ እንዳሉት ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና አማራን አንገት ለማስደፋት አልሞ እና አቅዶ ወረራ ቢያካሂድም ኢትዮጵያውያን ታይቶ በማይታወቅ አንድነት “ሆ” ብለው ተነስተው የሀገራቸውን ችግር ሊቀርፉ ሕመሟን ሊታመሙ ተሠልፈዋል፡፡ ጀግኖች በግንባር ጠላትን እየደመሰሱ ነው፤ ተማሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ደግሞ የደረሱ የዘማች አርሶ አደሮችን ምርት በአግባቡ እየሰበሰቡ ነው ብለዋል፡፡
አቶ አምሳሉ ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመደምሰስ ወደ ግንባር ያቀኑ ዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል መሰብሰቡ ቅድሚያ የተሠጠው ተግባር ነው፤ በዚህም እስካሁን አብዛኛው የዘማች አርሶ አደሮች ሰብል ተሰብስቧል ብለዋል፡፡
በሰብል ስብሰባው ወቅት የሚከሰትን የምርት ብክነት ለመቀነስም የባለሙያ ድጋፍ ከመኖሩ በተጨማሪ 84 ኮምባይነሮች ሥራ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎች፣ የመንግሥት ተቋማት ሠራተኞች እንዲሁም ማኅበረሰቡ ሰብል በመሰብሰብ ያደረገውን ትብብር በመስኖ እና በዳግም ሰብል ልማት ሥራው አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
