❝በኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያን በሚወዱ ኹሉ እገዛ የተጎዱ እና የወደሙ የጤና ተቋሞቻችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ መልሰን እንደምንገነባ አልጠራጠርም❞ ዶክተር ሊያ ታደሰ

132

ታኅሣሥ 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ ጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በማሰባሰብ እየተረባረቡ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዶክተር ሊያ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ❝በእናንተ እና ኢትዮጵያን በሚወዱ ኹሉ እገዛ የተጎዱ እና የወደሙ የጤና ተቋሞቻችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ መልሰን እንደምንገነባ አልጠራጠርም❞ ነው ያሉት።
በ’አንድ ሚሊዮን ወደ የሀገር ቤት’ ጥሪ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ የጤና ተቋማት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል ዘመቻ ተጀምሯል።
‘አንድ ሻንጣ ለወገኔ’ በሚል መሪ ሐሳብ የተጀመረው እንቅስቃሴ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዳያስፖራዎች የመድኃኒት ድጋፍ ይዘው እንዲመጡ የማድረግ ዓላማ ያለው መሆኑንም ተገልጿል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ በሺዎች በሚቆጠሩ የጤና ተቋማት ላይ በፈጸመው ውድመትና ዝርፊያ ምክንያት ዜጎችና ተቋማቱ ለችግር መጋለጣቸው ይታወቃል።
በርካታ ዜጎች የጤና አገልግሎት የሚያገኙባቸው የሕክምና ቁሳቁሶች ስለሚያስፈልጋቸው ወደ ሀገር ቤት የሚመጡ ዳያስፖራዎችም የሕክምና ግብዓቶችን ይዘው እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

Previous article“አፍሪካዊያንን በማሳተፍ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የውጭ ጣልቃገብነት ለማስቆም እየሠራን ነው” በደቡብ አፍሪካ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባልና የዩናይትድ ሚዲያ ሃውስ መስራች አቶ በኃይሉ መሐመድ
Next article“የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ውሳኔ ሰጥቶ ሸንጎ እንደመቀመጥ ነው” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት