የሃይማኖት መምህራን እና ዳኢዎች ለተፈናቃይ ወገኖች ከምግብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ ባለፈ የሥነ ልቦና ግንባታ ሥራዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቅረበ፡፡

203

ባሕርዳር፡ ታኅሣሥ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና አፋር ክልል የፈጸመው ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመትን በማውገዝ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ መልዓከ ሰላም ኤፍሬም ሙሉዓለም አሸባሪ ቡድኑ ንጹኃንን በመግደል፤ ሴቶችን በመድፈር፤ በርካታ ዜጎችን ከመኖሪያ ቀያቸው በማፈናቀል የሰቆቃ ኑሮ እንዲኖሩ ማድረጉን፣ ቤተ እምነቶችን ማውደሙን እና መዝረፉን እንዲሁም ሕዝብ የሚጠቀምባቸውን መሰረተ ልማቶችን ማውደሙን እና መዝረፉን በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ በፈጠረው እኩይ ተግባር ማዘናቸውን የገለጹት የጉባኤው ሰብሳቢ መልዓከ ሰላም ኤፍሬም ሙሉዓለም የጉዳቱ ሰለባ የሆኑትን ወገኖች የሕክምና፤ የሥነ ልቦና እና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን በማከናወን ሁሉም ቤተ እምነቶች ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከአሸባሪው ቡድን ነጻ የወጡ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እና ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያለው ማኅበረሰብ ጠንካራ ድጋፍ እንዲያደርግ ጉባኤው ጥሪ አድርጓል፡፡
መልዓከ ሰላም ኤፍሬም የዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ በአማራ እና አፋር ክልል በንጹኃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እና መከራ አይቶ እንዳላየ ማለፉ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤውን አሳዝኗል ብለዋል፡፡ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሴቶች እና ሕፃናት፤ በቤተ እምነቶች እና በሀገር መሰረተ ልማት ላይ አሸባሪ ቡድኑ እያደረሰ ያለውን ጥቃት እና ውድመት ተመልክቶ በማውገዝ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንዲያደርግ የሃይማኖት ጉባኤው ጠይቋል፡፡
ዘጋቢ፡-ባለ ዓለምየ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

Previous article“አማራጫችን ማሸነፍ ብቻ ነው” የወገን ጦር አባላት
Next article❝ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን መቀላቀላቸው ታሪክ ለክብር እንዳጫቸው ሊቆጥሩት ይገባል❞ አቶ ክርስቲያን ታደለ