
ታኅሣሥ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በ’አንድ ሚሊዮን ወደ የሀገር ቤት’ ጥሪ የጤና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል ዘመቻ ተጀመረ።
‘አንድ ሻንጣ ለወገኔ’ በሚል መሪ ሐሳብ የተጀመረው እንቅስቃሴ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዳያስፖራዎች የመድኃኒት ድጋፍ ይዘው እንዲመጡ የማድረግ ዓላማ ያለው መሆኑን የ’በቃ’ ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ አስተባባሪዎች የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ በሺዎች በሚቆጠሩ የጤና ተቋማት ላይ በፈጸመው ውድመትና ዝርፊያ ምክንያት ዜጎችና ተቋማቱ ለችግር መጋለጣቸውን ይታወቃል።
በርካታ ዜጎች የጤና አገልግሎት የሚያገኙባቸው የሕክምና ቁሳቁሶች ስለሚያስፈልጋቸው ወደ ሀገር ቤት የሚመጡ ዳያስፖራዎችም የሕክምና ግብዓቶችን ይዘው እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
መድኃኒቶች፣ የሕክምና መሳሪያዎችና ሌሎች የጤና መገልገያ እቃዎችን ይዘው በመምጣት የጤና ቁሳቁስ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖችና የጤና ተቋማት እንዲደርሱ ተጠይቋል።
ወደ ሀገር ቤት መምጣት የማይችሉ ዳያስፖራዎች ድጋፋቸውን በሌላ ሰው በማስላክ እንዲደግፉ የዘመቻው አስተባባሪዎች ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ዳያስፖራው የሚያመጣውን የጤና ቁሳቁስ ድጋፍ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በማሰባሰብ ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንደሚከፋፋልም አመልክተዋል።
እስከ አሁን ከ2 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት አገልግሎት እንደማይሰጡና በመንግሥት ተደራሽ ያልሆኑ አካባቢዎች ሲካተቱ ውድመት የደረሰባቸዉ የጤና ተቋማት ቁጥር ከዚህም እንደሚያሻቅብ የጤና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
