
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሕዝብ የሽምግልና ሥርዓት ማኅበር በሥነ ምግባር እና በግብረ ገብነት የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር ማድረግ ትልቁ ዓላማው መሆኑንም የማኅበሩ መሥራቾች ይናገራሉ፡፡
በአማራ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ግምት የሚሰጠውንና የችግር መፍቻ ቁልፍ የሆነው የሽምግልና ሥርዓት ትልቅ ድርሻ እንዲኖረው ይሠራል፡፡ ትውልዱ በኢትዮጵያዊነቱ ጸንቶ በአባቶቹ ታሪክ ኮርቶ እንዲኖር እንደሚሠራም ተገልጿል።
በወቅታዊ ጉዳይ ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የማኅበሩ አባላት የአማራ ሕዝብ በየዘመናቱ የተነሱበትን ጠላቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን #መደምሰሱን ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል ሕዝብ የሽምግልና ሥርዓት ማኅበር አባል አቶ ሂሩይ ደመላሽ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ብለው የመጡ ጠላቶችን በሕዝብ ርብርብ እየታገልናቸው ነው ብለዋል፡፡ አሸባሪውና ወራሪው ቡድን ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን መልሶ መገንባትና የተጎዱ ዜጎችን ለማቋቋም ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡ የሥነ ልቦና ችግር የደረሰባቸውን ወገኖችንም ማረጋጋት እንደሚገባ ነው የገለፁት፡፡ የነበረውን ለማስተካከል አለኝታው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የአማራ ሕዝብ ታላቅ ሕዝብ ነው ያሉት አቶ ሂሩይ ከአሁን በፊት በሀገር ላይ የተነሱ ጠላቶችን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ማሸነፉንና መመለሱን ተናግረዋል፡፡ አሁን የተነሳውን ጠላትም ያሸንፈዋል ነው ያሉት፡፡ የአማራ ሕዝብ ጠላትን በማሸነፍና ውድመት የደረሰበትን ለማስተካከል ወደኋላ የማይል ሕዝብ እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡
ሕዝቡ ጠላትን በመደምሰስ የተጎዳውን መሠረተ ልማት እንዲያቋቋምም አደራ ብለዋል፡፡ የትግራይ ወራሪና አሸባሪ ቡድን የሰውነት መንፈስ ይዞ ያልተነሳ፣ የውጭ ጠላቶችን ተልዕኮ ይዞ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እኩይ ድርጊት እየፈጸመ ያለ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የአማራ ሕዝብ በትጋት ጠላቱን ማሸነፍና መምታት እንደሚገባውም ገልጸዋል፡፡

ሌላኛው የማኅበሩ አባል ሼህ ከድር ያሲን አሸባሪውና ወራሪው ቡድን በእንቢተኝነት ሀገርን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳ ሰይጣናዊ ሥራ የሚሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሀገርን ለማፍረስ የተነሳውን ጠላት በጋራ #ማጥፋት ይገባል ብለዋል፡፡ ሕዝቡ በችግር ውስጥ እንዳይኖር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አባቶቻችን በደምና በአጥንት ያቆዩዋትን ሀገር ወጣቶች የአባቶችን አርዓያ በመከተል ጠላትን ድል ማድረግ ይገባቸዋልም ነው ያሉት፡፡
የአማራ ክልል ሕዝብ የሽምግልና ሥርዓት ማኅበር ለወገን ጦር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
