የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በደሴና ኮምቦልቻ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ላይ የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ያደረሰውን ውድመት በጥናት ይፋ አደረገ።

216

አዲስ አበባ፡ ታኅሣሥ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በደሴና ኮምቦልቻ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ላይ የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ያደረሰውን ውድመት በቦታው ተገኝቶ ያጠናውን የጥናት ውጤት ይፋ አደረገ። ባለፈው ሳምንት በሰሜን ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች አሸባሪው ቡድን ያደረሰውን ውድመት በተመለከተ ጋዜጠኞች ወደስፍራው እንዲጓዙና ምልከታቸውንም ያካተተ ጥናት ይደረጋል በተባለው መሰረት ጥናት ተደርጓል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሸባሪው ትህነግ በወረራ ይዟቸው በነበሩት ደሴና ኮምቦልቻ የሚገኙ 40 ኢንዱስትሪዎች ላይ ውድመት አድርሷል።
እነዚህ ውድመቶች ታስቦባቸው እንደተፈጸሙ ገልጸዋል። በቁጥርም 8 ከፍተኛ (ሙሉ በሙሉ) 8 መካከለኛ 24 አነስተኛ ወይም የተወሰነ ጥገና ተደርጎ ወደ ስራ ሊመለሱ የሚችሉ ናቸው።
ኢንዱስትሪዎቹ ከ11 ሺ በላይ የስራ እድል የፈጠሩ በመሆኑ ብዙዎች ከስራ ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ማድረጉን ነው ሚኒስትሩ ያብራሩት።
ይህንን ጉዳት ተገንዝቦ እንደየጉዳት መጠናቸው የተለዩትን ወደስራ ለማስገባት የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውንም ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገልጸዋል። ከሰኞ ጀምሮም ባለሙያዎች ወደስፍራው እንዲሰማሩና በፍጥነት ተስተካክለው ወደስራ የሚገቡትን ስራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ ተጀምሯል ነው የተባለው።
ዘጋቢ፡- ድልነሳ መንግስቴ- ከአዲስ አበባ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporati

Previous articleፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት አቢጃን ከተማ ገቡ።
Next articleየአማራ ክልል ሕዝብ የሽምግልና ሥርዓት ማኅበር በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት መረባረብ እንደሚገባ ገለጸ።