የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በአማራ ክልል ታኅሣሥ 08/2014 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

183

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ነገ የሚካሄደዉ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ የአማራ ክልል ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ መግለጫ ሰጥቷል።
የአማራ ክልል ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ አስናቁ ደረስ የሰላማዊ ሰልፉ ዋና ዓላማ አሸባሪው ቡድን በአማራና በአፋር ክልሎች በሴቶች፣ ሕፃናት እና አረጋውያን ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ በማውገዝ ተጠያቂ እንዲኾን ለመጠየቅ እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡ በሰልፉ ላይ አንዳንድ ምእራባውያን ሀገራት በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብነትን እንዲያቆሙ መልእክት እንደሚተላለፍም አብራርተዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ ወረራ በፈጸመበት በአማራና በአፋር ክልሎች በርካታ ሴቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን አሰቃቂ ግፍ እንደተፈጸመባቸው ወይዘሮ አስናቁ ጠቁመዋል።
ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ሕጉን ያወጡት አንዳንድ ምእራባውያን ሀገራት በሽብር ቡድኑ እየተጣሱ ያሉ ሕግጋትን ጀሮ ዳባ ልበስ ብለው ማለፋቸውን ተናግረዋል፤ አንዳንድ ምእራባውያን ሀገራት የሽብር ቡድኑን ማውገዝ ሲገባቸው ድርጊቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሲያበረታቱትና ሕጋዊውን መንግሥት ለማፍረስ ሲጥሩ ይታያሉም ብለዋል። በሰላማዊ ሰልፉ የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት እንዲቆም መልእክት እንደሚተላለፍ ነው የጠቆሙት። ኀላፊዋ እንዳሉት ችግሩ መፍትሔ እስኪያገኝ ድረስ የሚደረገው ጫና ተጠናክሮ ይቀጥላል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ የሻረግ ፈንታሁን ሴቶችን ጨምሮ ሁሉም የማኅበረብ ክፍሎች በወገን ላይ የሚደርሰውን ግፍ ሊያስቆሙት ይገባል ብለዋል። አረመኔው ቡድን በተለይ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ላይ አሰቃቂ ድርጊቶችን እየፈጸመ እንደሚገኝም አስረድተዋል። ኀላፊዋ በሰላማዊ ሰልፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፉበታል ነው ያሉት።
ሰላዊ ሰልፉ አንዳንድ ምእራባውያን ሀገራት እይታቸውን እንዲያስተካክሉ የሚያስችል መልእክት ያገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው ያላቸውን እምነት የተናገሩት፡፡ በመኾኑም ነገ በባሕር ዳር ከተማ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት በሚካሄደው ክልላዊ ሰላማዊ ሰልፍ መላው ኅብረተሰብ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ኀላፊዋ ጥሪ አድርገዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ቡሩክ ተሾመ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleኢትዮጵያ ዓለምን አስተምራ በአፍሪካ ተምሳሌት የምትሆንበት ጊዜ መቃረቡን የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
Next articleፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት አቢጃን ከተማ ገቡ።