ኢትዮጵያ ዓለምን አስተምራ በአፍሪካ ተምሳሌት የምትሆንበት ጊዜ መቃረቡን የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

131

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በፈጸመው ወረራ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ ተጀምሯል፡፡ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን እንዳስታወቀው በሂደቱ ማኅበረሰቡ ለረሃብ እንዳይጋለጥ አስቸኳይ ምግብ ከማድረስ ባለፈ በወረራው ምክንያት የደረሰውን የጉዳት መጠን መሠረት በማድረግም ሕዝቡን መልሶ የማደራጀት እና በዘላቂነት የማቋቋም ሥራ በመረጃ ላይ ተመሥርቶ እንደሚከናወን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ እያሱ መስፍን ተናግረዋል፡፡
አምርቶ ራሱን እስከሚችል ድረስ ሁለንተናዊ ድጋፉ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በቋሚነት መልሶ የማቋቋም ተግባሩ የመላው ኢትዮጵያውያን ርብርብ ይሻል፡፡ የወደሙ ቤቶችን መልሶ መገንባትን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ የመልሶ ግንባታ እስትራቴጂ የተነደፈ መሆኑን ያነሱት አቶ እያሱ የኢትዮጵያውያን በችግር ጊዜ የመረዳዳት እሴት የአሁናዊ ችግራችን መሸጋገሪያ ድልድይ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች የገቡትን ቃል ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ተግባራዊ አለማድረጋቸው አሳፋሪና የሚያስተዛዝብ ሆኗል፡፡ አሸባሪው ቡድን በፈጸመው የግፍ ወረራ ምክንያት የደረሰውን ቀውስ አስመልክቶ በልዩ ልዩ መንገድ የማስረዳት ሥራ ቢከናወንም እነዚህ የእርዳታ ድርጅቶች አይተው እንዳላዩ፣ ሰምተውም እንዳልሰሙ ሆነው አልፈዋል፡፡ ይባስ ብሎ የአንድ ሀገርን ሕዝብ ነጣጥለው ለመርዳት ያሳዩት እንቅስቃሴ ተገቢ ካለመሆኑም ባሻገር በሕዝብ ችግር እንደመሳለቅ ይቆጠራል ብለዋል አቶ እያሱ፡፡ ከስሕተታቸው ትምህርት መውሰድ ከቻሉ ግን አሁንም እድሉ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ኢትዮጵያውያን በመረባረብ ዓለምን አስተምረው ለአፍሪካ ተምሳሌት ሆነው የሚቀጥሉበት ጊዜ መቃረቡ አጠራጣሪ አይደለም ብለዋል፡፡ ችግሩን ለማለፍ እጅን አጣጥፎ የውጪ ሀገራትን ችሮታ የሚጠብቅ ሳይሆን እርስ በራሱ ተረዳድቶ ተዓምር መስራት እንደሚችል ያሳያል ነው ያሉት፡፡ ለዚህም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ግለሰቦች እና ነጋዴዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተለመደ ኢትዮጵያዊ ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ እያሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleበአሜሪካ እና በአውሮፓ የሚኖሩ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት የአየር እና የምድር ኃይል አባላት የሀገራቸውን ጥሪ በመቀበል በሙያቸው ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡
Next articleየውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በአማራ ክልል ታኅሣሥ 08/2014 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡