በአሜሪካ እና በአውሮፓ የሚኖሩ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት የአየር እና የምድር ኃይል አባላት የሀገራቸውን ጥሪ በመቀበል በሙያቸው ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

251

ታኅሣሥ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ እና በአውሮፓ የሚኖሩ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት የአየር እና የምድር ኃይል አባላት የሀገራቸውን ጥሪ በመቀበል በሙያቸው ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት እንዳሉት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የሚያካሂደው የውክልና ጦርነት እና የውጭ ሀገራት ጫናን እንመክታለን፤ እኛ ልጆቿ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም ነው ያሉት፡፡ ከጀግናው የወገን ጦር ጎን ተሰልፈው በሙያቸው ለማገልገል ከመቸውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
ሀገር ወዳድ የሠራዊት አባላት ከዚህ በፊት በአሸባሪው ቡድን ምክንያት ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ወደ በግንባር በመዝመት የሽብር ቡድኑን በመደምሰስ የኢትዮጵያን ውድቀት ለማየት የቋመጡ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራትን ለማሳፈር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ “ጠላቶች ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት ብለው እንደ አሸን በፈሉበት በዚህ ወቅት ልጆቿ መስዋእትነት በመክፈል የጠላትን አንገት እያስደፉ ይገኛሉ” ነው ያሉት፡፡ ይህም የጠላቶቻችንንም ኾነ የወዳጆቻችንን እጅ በግርምት አፍ ላይ ያስጫነ ድንቅ የጀግንነት ተግባር ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን ለማገልገል መመረጥ በራሱ እድለኝነት በመሆኑ ሁሉም አባላት ሙያቸው እና ሙያዊ ስነምግባራቸው በሚፈቅድላቸው መልኩ መሰማራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ሀገር ወዳድ የኢትዮጵያ ልጆች በመሆናቸውም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleየተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ ላይ የጠራዉ ስብሰባ ወቅትን ያላገናዘበና የኢትዮጵያን አቋም የሚቃረን ነው ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
Next articleኢትዮጵያ ዓለምን አስተምራ በአፍሪካ ተምሳሌት የምትሆንበት ጊዜ መቃረቡን የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡