
ባሕር ዳር፡ መስከረም 24/2012 ዓ/ም (አብመድ) የፌዴራል የገቢዎች ሚኒስቴር የባሕር ዳር ቅርንጫፍ በአማራ ክልል ለሚገኙ 5 ግብር ከፋዮች ዕውቅና እየሰጠ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳሁን ደመመ ዕውቅናው ሌሎች በክልሉ የሚገኙ ነጋዴዎችንና ሠራተኞችን የሚያበረታታ መሆኑን ተናረዋል፡፡
ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በሚያዘጋጀው መድረክ ‹‹በክልሉ የሚገኙ ግብር ከፋዮች እና ሠራተኞች ይመሠገኑበታል፤ ነጋዴዎች ግብር በመክፈላቸው እንዲኮሩ እና ለሌሎች ነጋዴዎች አርአያ እንዲሆኑ ያሰችላል›› ብለዋል፡፡
የዕውቅና መድረኩ አሁን በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ዝርዝር መረጃዎችን የምናደርስ ይሆናል፡፡
ዘጋቢ፡- ብሩክ ተሾመ