
ታኅሣሥ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪዉ የትግራይ ወራሪ ቡድን ዝርፊያና ዉድመት የደረሰበት የሐይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በአጭር ጊዜ ዉስጥ አገልግሎት እንዲሰጥ አስፈላጊውን እገዛ እናደርጋለን ሲሉ የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደዉ ገለጹ።
የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደዉ እንደገለጹት፤ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የሐይቅ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታልን እንዲያቋቁም ከጤና ሚኒስቴር ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ኃላፊነቱን በመወጣት ሆስፒታሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ እንዲገባ በሰዉ ኃይል፣ በመድኃኒትና በሕክምና ዕቃዎች ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት ተደርጓል።
የህክምና አገልግሎት ጊዜ የሚሰጥ አይደለም ያሉት ዶክተር ያሬድ፤ የምትወልድ እናት፣ አጣዳፊ ሕመም ያለበትና ድንገተኛ ሕክምና የሚፈልጉ ዜጎች በስፍራው ይገኛሉ። ስለሆነም ሆስፒታሉ በአፋጣኝ ሥራ የሚጀምርበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ጥረት ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።
እኔ የምመራው ልዑክ ከዛሬ ጀምሮ ጉዳት የደረሰበት የሐይቅ ሆስፒታልን ይጎበኛል። ከጉብኝቱ ጋር በተያያዘ እንደ መድኃኒት፣ የሕክምና ዕቃዎችና ማሽኖች እንዲሁም ሌሎች ሆስፒታሉን ሥራ ለማስጀመር የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በመጀመሪያ ዙር ለሆስፒታሉ ይደርሳሉ ብለዋል።
ሆስፒታሉ በፍጥነት ወደ አገልግሎት እንዲመለስ የሚረዱ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል፡፡ የሕክምና ዕቃዎቹ በሆስፒታሉ እንደደረሱም አካባቢውን በማጽዳት ሆስፒታሉ ዳግም አገልግሎት እንዲጀምር ጥረት ይደረጋል ሲሉ አስታውቀዋል።
በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኩል ተቋሙን ለማደስ እንዲሁም መልሶ ለማቋቋም የፕሮቶኮል መመሪያ አለ። በዚህ መመሪያ መሰረት መጀመሪያ ትኩረት የሚሰጠዉና አገልግሎት የሚጀምሩት የተመላላሽ ሕክምና ክፍል፣ የእናቶችና ሕጻናት፣ የወሊድ ክፍል እንዲሁም የድንገተኛ ክፍሎች መሆናቸውን እንደተገለጸ ኢፕድ ዘግቧል።
እንደ ዶክተር ያሬድ ገለጻ፤ አሸባሪዉ የትግራይ ወራሪ ቡድን በተለይ በሆስፒታሎች ያደረሰዉ ዉድመት ኾነ ተብሎ ማኅበረሰቡን በተዘዋዋሪ የመግደል ዘመቻ ነዉ። የሕክምና መሣሪያዎችን ሰርቆ የማይችሉትን ደግሞ አዉድሞ መሄድ ማኅበረሰቡን ለመጉዳት ያለመ እና ከሰዉ ልጅ የማይጠበቅ አሳፋሪ ተግባር ነዉ። በአፍሪካና በማደግ ላይ ባለች ሀገር ዉስጥ በተለይ በገጠራማ አካባቢዎች ሰዎች በጣም ብዙ ኪሎ ሜትር ተጉዘዉ የሚታከሙበትን ተቋም ኾን ብሎ ማዉደም ከባድ ወንጀል ነዉ ብለዋል።
ከዚህ በኋላ ስለ ጥፋቱና ዉድመቱ ብቻ እያወራን ጊዜ ማጥፋት የለብንም። ቡድኑ በጤና ተቋማት ላይ ውድመት ቢያስከትልም በተባበረ ክንድ መልሰን ሥራ እንዲጀምሩ እናደርጋለን። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዉድመቱ በደረሰባቸዉ ከአማራና አፋር ክልል ማኀበረሰብ ጋር በመተባበር ወገቡን ታጥቆ ከዚህ በፊት ከነበሩን የተሻሉ ተቋማትን መገንባት እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የጤና ባለሙያዉ፣ባለሀብቱ እንዲሁም ኹሉም ኢትዮጵያዊ ያለዉን ድጋፍ ቢያደርግ የወደመዉን መልሰን መገንባት አያቅትም። “ኃላፊነታችንን በመወጣት ሠርተን የማሳየት እልህ ዉስጥ ገብተናል፤ እናደርገዋለንም” ነው ያሉት።
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
