“በካሳጊታ በከባድ መሳሪያ ተመተው የወደቁ ምሰሶዎችን መልሶ የመትከል ሥራ ተጠናቋል” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

196

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን መልሶ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠሉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመር ጥገና የቴክኒክ ድጋፍ ኃላፊ ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው አቶ ተስፋዬ መንግስቱ እንደተናገሩት የደረሱ ጉዳቶችን በመለየትና በፍጥነት መልሶ በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በተቋሙ ዘጠኙም ሪጅኖች ያሉ የጥገና ባለሙያዎች በቅንጅት በመሥራት ላይ ናቸው፡፡
የጥገና ቡድኑ ሥራውን ለማቀላጠፍ በሦስት አቅጣጫዎች – በጋሸና፣ በኮምቦልቻና በሚሌ መስመሮች ተከፋፍሎ እየሰራ መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡
በኮምቦልቻ መስመር ጥገናውን እያከናወነ ያለው ቡድን ባከናወናቸው የመልሶ ጥገና ሥራዎች ከሸዋ ሮቢት እስከ ደሴ ያሉ ከተሞች እንዲሁም ወደ አቀስታ መስመር ያሉ ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል፡፡
በሚሌ በኩል ያለውን የጥገና ሥራ የሚያስተባብሩት የምሥራቅ ሪጅን ትራንስሚሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ዳይሬክተር አቶ ጋሻው እንድሪያስ በበኩላቸው የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነና ከጠበቁት በላይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ከካሳጊታ እስከ ኤሊውኃ 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው መስመር ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና መስመሩን በአብዛኛው እንደአዲስ የመዘርጋት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በካሳጊታ በከባድ መሳሪያ ተመተው የወደቁ ሶስት ምሰሶዎችን መልሶ የመትከል ሥራ መጠናቀቁንም ገልፀዋል፡፡
ከኮምቦልቻ ሠመራ የሚሔደውን ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የጥገና ሥራውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በአራት ቡድኖች ተከፋፍሎ ሁሉም ተናቦ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
የጥገና ቡድኑ ሥራውን በፍጥነት ለማጠናቀቅና በበርካታ የአፋር ከተሞች የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማስጀመር በትጋት እየተሰራ ነው፡፡
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተቋምን በመቀላቀል ሀገራቸውን ከማንኛውም ጥቃት የመከላከል ታሪካዊ አደራ እንዳለባቸው የቀድሞ የሠራዊት አባላት ገለጹ።
Next articleበወራሪው የጠላት ኃይል ላይ መንግሥት እየወሰደ ካለው የተጠናከረ የማጥቃት እርምጃ ጎን ለጎን በሀገሪቱ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቋቋም እና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ።