
ታኅሣሥ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞ የሠራዊት አባሉ ምክትል አስር አለቃ ዳውድ ደሳለኝ ለ13 ዓመታት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ተቋም ውስጥ አገልግለዋል። በዚህ ወቅትም የአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ሀገር የማፍረስ ዓላማ ለማክሸፍ በዋግ ግንባር የሚገኘውን የወገን ጦር ተቀላቅለዋል። ልጃቸውም ተቋሙን መቀላቀሉን ነግረውናል። የመከላከያ ተቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና ትላልቅ ባለሙያዎችን ያፈራ፣ በማፍራት ላይም የሚገኝ ተቋም እንደኾነ ገልጸዋል። ተቋሙ የተለያዩ የሙያ ዘርፎችን በመቅሰም ከራስ ባለፈ ለሀገር ዕድገት ትልቅ አቅም መፍጠር የሚያስችል እንደኾነም ነግረውናል። ወጣቶች ይህንን በመገንዘብ ተቋሙን መቀላቀል እንደሚገባም መክረዋል።
ምክትል አስር አለቃ ጸጋው አድማሴም ለረጅም ጊዜ በውትድርና ሀገራቸውን አገልግለዋል። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የሀገር አለኝታ የኾነውን ሠራዊት በትኖ ጥላቻውን በገሃድ ማሳየቱን ያነሱት ምክትል አስር አለቃ ጸጋው አሁን ላይ የፈጸመውን ክህደት ለመመከት ግንባር መሰለፋቸውን ገልጸዋል። ጠንካራ ሀገር መገንባት የሚቻለው ጠንካራ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ደኅንነት መገንባት ሲቻል መኾኑን ያነሱት ምክትል አስር አለቃ ጸጋው ወጣቶች ይህንን ተገንዝበው የመከላከያ ተቋምን በመቀላቀል ከውጭ እና ከውስጥ የሚቃጣን ማንኛውም ትንኮሳ የመከላከል ታሪካዊ ግዴታ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ወታደር ታደሰ መለሰ መከላከያ ተቋም የሀገር አለኝታ የኾኑ ትልልቅ ሙያተኞችን ያፈራ ታላቅ ተቋም በመኾኑ ወጣቶችም ተቋሙን በመቀላቀል ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ መክረዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
 
             
  
		