❝የአማራ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ትቀላቀሉ ዘንድ ዛሬም ጥሪዬን አቀርብላችኋለሁ❞ አቶ ክርስቲያን ታደለ

321

ታኅሣሥ 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ❝የአማራ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ትቀላቀሉ ዘንድ ዛሬም ጥሪዬን አቀርብላችኋለሁ❞ ብለዋል።
አቶ ክርስቲያን ታደለ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ክርስቲያን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ❝ድል ማድረግ ትፈልጋለህ? ሀገርህ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ትፈልጋለህ? ሕዝብህን የሰፈር ጎረምሳ እንዳይፈነጭበት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ወንድሜ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ተቀላቀል! እመነኝ አስከብረኸን፥አንተም በሙያህ ተከብረህ ትኖራለህ። እህቴ መልእክቱ ለአንቺም ነው። በተለይ የአማራ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ትቀላቀሉ ዘንድ ዛሬም ጥሪዬን አቀርብላችኋለሁ❞ ነው ያሉት።
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በጋሸና ግንባር ለወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ፡፡
Next article“የሽብር ቡድኑ ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ደሴ ቅርንጫፍ ከ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሃብት ዘርፏል፤ አውድሟል” ኤጀንሲው