
ታኅሣሥ 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በጋሸና ግንባር በመገኘት ለጀግናው የወገን ጦር 5 ሚሊየን ብር የሚገመቱ 53 ሰንጋዎችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ድጋፉን ለወገን ጦር አስረክበዋል፡፡
አምባሳደሯ እንዳሉት ሚኒስቴሩ በዲፕሎማሲው ግንባር ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና እየተፋለመ ይገኛል፤ ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ ከዚህ ባለፈም በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው የወገን ጦር ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡
በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የተለያዩ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
በግንባሩ ድጋፉን የተረከቡት ብርጋዴር ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱ ድጋፉ ለሠራዊቱ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡ “ሕዝባችን የሰጠንን አደራ እንወጣለን፤ አሸባሪው ቡድን ይደመሰሳል፤ ኢትዮጵያ በአሸናፊነቷ ትቀጥላለች” ነው ያሉት፡፡
ዘጋቢ፡- ቢኒያም መስፍን -ከጋሸና ግንባር
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
 
             
  
		