የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ የተነሱ ዐበይት ጉዳዮች፡፡

439

ታኅሣሥ 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
-የዋጋግሽበትን ለማረጋጋት በመንግሥት በተወሰዱ ልዩ ልዩ ርምጃዎች በባለፉት ሁለት ወራት በተለይ በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የሚያስችሉ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡
-ምግብ ነክ ባልሆኑት ላይ ግን የዋጋ ግሽበቱ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ይህም ምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ግሽበቱን ለማረጋጋት የተወሰዱትን አይነት ርምጃዎች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አመላካች እንደሆነ ተነስቷል፡፡
-የዋጋ ግሽበቱን ወደ ነጠላ አሐዝ ለማድረስ የሀገር ውስጥ ምርትን መጨመር እና የሸቀጦች አቅርቦት በበቂ ደረጃ ማሳደግ የሚል የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
-የትኩረት አቅጣጫው የገበያ ሰንሰለቱ ከአሻጥር ነጻ ማድረግንም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
-በ2014 በጀት ዓመት መጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት የፌዴራል መንግሥቱ የታክስ ገቢ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ወደ 10 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ አሳጥቷል፡፡
-አጠቃላይ ወጪው ደግሞ በ22 ነጥብ 7 በመቶ ጨምሯል፡፡
-የመደበኛ ወጪ በ34 በመቶ እንዲሁም የካፒታል ወጪው ደግሞ 4 በመቶ ጭማሪ የታየባቸው የፌዴራል መንግሥት ወጪ ናቸው፡፡
-በመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት የሸቀጦች የወጪ ንግድ ወደ 16 በመቶ ጭማሪ ያስመዘገበ ሲሆን ወደ 972 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ገቢ አስገኝቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ ቡና ከፍተኛውን ድርሻ ሲይዝ አትክልትና ፍራፍሬ ተከታዩን ደረጃ ይይዛሉ፡፡
-በሦስት ወራቱ ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ አሳይቷል፡፡
-የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መጨመሩ እና ግሽበትን ለመቀነስ የተወሰዱ ማሻሻያዎች የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ መሸከም የሚያስችል ኢኮኖሚ ለመገንባትና ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች የመልሶ ግንባታ ለማፋጠን ያግዛል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብhttps://bit.ly/2RnNHCq
http://xn--amharaweb-u80b8u3b7lt0cho.com/
በቴሌግራምhttps://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተርhttps://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleየአማራ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች በዋግ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ።
Next articleበስፔን ባርሴሎና የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ የውጭ ሀገራትን ጣልቃገብነት ተቃውመዋል።