
ታኅሣሥ 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የግዥ፣ ሎጀስቲክስ፣ ንብረት አስተዳደር እና ፋሲሊቲ ሥራ አስኪያጅ ይሄነው መንግሥቱ እንደነገሩን የተቋሙ ሰራተኞች ከ700 ሺህ ብር በላይ ከደመወዛቸው በማዋጣት የሰንጋ፣ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣ የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል። በቀጣይም በሌሎች ግንባሮች ድጋፍ እንደሚያደርጉ ነግረውናል።
ድጋፉ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እስኪደመሰስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የተቋሙ ሰራተኞች ከዚህ በፊትም ለመከላከያ ሰራዊት ከደመወዛቸው ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል። ግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው የወገን ጦር የደም ልገሳም ተደርጓል።
ከወራሪው ነጻ በኾኑ አካባቢዎች ማኅበረሰቡን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑንም አንስተዋል። በዋግ ግንባር ኮሎኔል ካሳ መኳንንት የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች ላደረጉት ድጋፍ አመስግነው ይህም ሰራዊቱ በተጠናከረ መንገድ ግዳጁን እንዲወጣ የበለጠ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። ድጋፉ የሰራዊቱን ሕዝባዊነት የበለጠ ስለሚያጠናክር እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
የወገን ጦር በጭላ ላይ በተካሄደው ጦርነት በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ ማድረሱን ኮሎኔል ካሳ ገልጸዋል።
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ ተስፋየ ገብሬ እንዳሉት የጸጥታ ኀይሉ ከሚያደርገው ትግል ባለፈ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስንቅ በማዘጋጀት፣ ምሽግ ድረስ ስንቅ በማቅረብ እና መሰል ሥራዎችን በመሥራት ደጀንነታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።
ዘጋቢ፦ዳግማዊ ተሠራ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
