የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

129

ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የተለያዩ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፎችን አድርጓል።

ድጋፉንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና አምባሳደሮች አስረክበዋል።

በርክብቡ ወቅት የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ “ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይህን ድጋፍ ሲያደርግ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እኩይ ድርጊት ከተጎዱ ወገኖች ጎን መሆኑን ለማሳየት ነው ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኅልውና ዘመቻው ከጀመረ ማግስት ጀምሮ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ተጋድሎ እያደረገ መሆኑን ያስታወሱት አምባሳደሯ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ የተቀናጀ ሥራ እየሠራ መምጣቱን ጠቁመዋል።

የተሰባሰበው ድጋፍም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት፣ ተጠሪ ተቋማትና ከውጭ ከሚገኙ የሚሲዮን ዲፕሎማቶች የተሰበሰበ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስቴሩ ከብሔራዊ ኮሚቴ ጋር በመሆን ለመከላከያ ሠራዊት እና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚሆን ድጋፍ በሁሉም ሚሲዮኖች በኩል እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleበጃማይካ የራስተፈሪያን ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የውጭ ጣልቃ ገብነት ተቃወሙ።
Next articleግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያውያን መብቶች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።