
ታኅሣስ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጃማይካ የራስተፈሪያን ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የውጭ ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
ኢትዮጵያውያን፣ ራስተፈሪያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በተሳተፉበት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ሰልፈኞቹ በኪንግስተን የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ድምጻቸውን አሰምተዋል።
የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ መንግሥት እያካሄደ ላለው የኅልውና ዘመቻ እንደሚደግፉም አረጋግጠዋል።
የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጣልቃገብነት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።
አሜሪካ እና አጋሮቿ የሽብር ቡድኑን በመደገፍ የያዙት አቋም እንዳሳዘናቸው የገለፁት ሰልፈኞቹ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግሥት ላይ እየተደረገ ያለውን ያልተገባ ጫናን አውግዘዋል።
ኢትዮጵያን ከአጉዋ በማስወጣት አሜሪካ የወሰደችው እርምጃ ተቃውመዋል። የአሜሪካ መንግሥት የያዘው የተዛባ አቋሙን እንዲያስተካክል ጠይቀዋል።
የግዛት አንድነትን የሚፈታተኑ የውጭ ጣልቃገብነቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
 
             
  
		