
ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “ዘመን ባስ” ከሸዋሮቢት፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ እና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ለ10 ቀናት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
የ“ዘመን ባስ” የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እይላቸው አያና እንዳስታወቁት ሕዝብን ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ ዋንኛ ሥራው የሆነው ተቋማቸው፤ በግፍ ተከብረውና ተወደው ከሚኖሩበት አካባቢያቸው በአሸባሪው ቡድን ተፈናቅለው በአዲስ አበባ እና በሌሎች ማቆያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች አገልግሎቱን ከነገ ጀምሮ ለመስጠት መወሰኑን ገልፀዋል።
ዛሬም ከሁለት አውቶብስ በላይ ተፈናቃዮች ተመዝግበው ነገ ጠዋት ጉዞ እንደሚጀምሩ ነው ኃላፊው ጨምረው የገለፁት።
ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ለእናቶች እና ለሕጻናት ቅድሚያ እንደሚሰጥ የገለፁት ኃላፊው ማንኛውም መታወቂያ የያዘ ግለሰብ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ላምበረት ከሚገኘው መናኸሪያ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል አስታውቀዋል።
አገልግሎቱን ለማግኘት በ“ዘመን ባስ” የትኬት መቁረጫ ቢሮዎች ሜክሲኮ፣ መስቀል አደባባይ እና ላምበረት መናህሪያ በሚገኙ ቢሮዎች መመዝገብ እንደሚቻልም ተገልጿል።
“ዘመን ባስ” ከዚህ ቀደምም ለኅልውና ዘመቻው ድጋፍ ሲያደርግ እንደቆየ እና በሌሎች ተመሳሳይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይም ተሰማርቶ መቆየቱን ነው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ለኢብኮ ገልጸዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
 
             
  
		