የአማራ ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል ጠላትን እንዲያጠፉና ሀገርን በዘላቂነት እንዲያስከብሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ጥሪ አቀረቡ፡

128

ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ወጣቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ በባሕር ዳር ከተማ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር ተባባሪ ፕሮፌሰር ፈንታሁን አየለ (ዶ.ር) በውይይቱ ወቅት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ግንባታን በተመለከተ ባቀረቡት ጽሑፍ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የተቃጡባትን ወረራና የተቀለበሰበትን መንገድ አንስተዋል፡፡ ከ16ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን የተሰነዘሩ ሦስት የወረራ ሙከራዎችን በማሳያነት አንስተዋል፡፡ ወታደር ኾነው ሀገራቸውን የመሩ በርካቶችን በማንሳት የውትድርና የሙያ ክብርን ጠቅሰዋል፡፡

በውይይቱ ተሳታፊ ከኾኑ ወጣቶች መካከል ኃይለኢየሱስ አለኸኝ የተጋረጠብንን አደጋ ለመቀልበስ ወጣቶች በመሪዎቹ የሚሰጡ ሐሳቦችን ተግባራዊ ማድረግ አለበት ብሏል፡፡

ወጣቶች ለሀገራቸው ማድረግ ስለሚጠበቅባቸው ኃላፊነት የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች በተከታታይነት መሠራት እንዳለባቸውም ጠቅሷል፡፡

ከአዊ ብሄረሰብ አስተዳር ዞን የውይይቱ ተሳታፊ በሪሁን ተፈራ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ከፍተኛ አደጋ በተጋረጠባት በዚህ ወቅት አንድ ኾነን በመደማመጥ ችግሩን የምንቀለብስበት ጊዜ ነው ብሏል፡፡ በርካታ ግንባሮች ያሉ ቢሆንም ለመዝመትም ዝግጁ ኾኜ እየተጠባበኩ እገኛለሁ ነው ያለው፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን መቀላቀል ከክብሮች ሁሉ ክብር መሆኑን ገልጿል፡፡

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ሐሰን ኢብራሂም “ጠላትህ ጠላት ብሎ ፈርጆ ሲመጣ አንተም ጠላትህን ለመመከትና አጸፋ ለመስጠት መዘጋጀት አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡ የአማራ ወጣቶች አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጠላት ብሎ የፈረጀው አማራን መሆኑን ተረድተው ጠላትን ለማሸነፍና ሀገርን በዘላቂነት ለማስቀጠል መከላከያ ሠራዊትን መቀላቀል አለባቸው ነው ያሉት፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በውይይቱ እንዳነሱት አሁን ባለው የህልውና ዘመቻ ጠላትን በተግባር መፋለም ያስፈልጋል፡፡ አሸባሪው የትግራይ ቡድን ኢትዮጵያን ማፍረስ፣ አማራን በሥነልቦና፣ በፖለቲካና በኢኮኖሚ ማዳክምና ሀብት መዝረፍ ዓላማው አድርጎ ወረራ እንደፈጸመም ገልጸዋል፡፡ ይህንን ወረራ በመቀልበስ ጀግኖች እየተዋደቁ ነው ያሉት አቶ ገዱ ድልም እየተገኘ ያለው በመደራጀት ስለሆነ ወጣቶች ተደራጅተው እንዲታገሉ ጠይቀዋል፡፡

የሀገር ውስጥም ኾነ የውጭ ጠላትን መመከት የሚቻለው በጠንካራ የመከላከያ ኃይል እንደሆነ የገለጹት አቶ ገዱ የአማራ ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል ጠላትን #እንዲያጠፉና ሀገርን በዘላቂነት እንዲያስከብሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀን አምባቸው

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleየፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ፡
Next articleበአማራና አፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በለንደን ተካሄደ፡፡