የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ፡

114

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ፡፡

ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ)የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በድምሩ ከ28 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ በወሎ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦር አድርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ አበበ ምክር ቤቱ 18 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳንዶካን ደበበ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ 10 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ እንዳደረጉ አመላክተዋል፡፡

በግንባር የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት ኮሎኔል ሙስጦፋ የሱፍ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ሕዝቡ እያደረገ ያለው የደጀንነት ተግባርን አድንቀዋል፡፡

እየተደረገ ያለው ድጋፍ የወገን ጦር ጉዞ የተሳካ እንዲሆን ያግዛል ነው ያሉት፡፡

ከመላ ኢትዮጵያውያን እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ድጋፉን ያደረጉት ተቋማት በቀጣይ ከወገን ጦር ጎን በመሆን አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ -ከወሎ ግንባር

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleየኢንስትራክተር እንዳልክ ቀለመወርቅ መታሰቢያና በአዲስ አበባ የካዛንችስ አብሮ አደግ ጓደኛሞች ማኅበር ለወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ፡፡
Next articleየአማራ ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል ጠላትን እንዲያጠፉና ሀገርን በዘላቂነት እንዲያስከብሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ጥሪ አቀረቡ፡