የኢንስትራክተር እንዳልክ ቀለመወርቅ መታሰቢያና በአዲስ አበባ የካዛንችስ አብሮ አደግ ጓደኛሞች ማኅበር ለወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ፡፡

117

የኢንስትራክተር እንዳልክ ቀለመወርቅ መታሰቢያና በአዲስ አበባ የካዛንችስ አብሮ አደግ ጓደኛሞች ማኅበር ለወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ፡፡

ጎንደር: ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ)የኢንስትራክተር እንዳልክ ቀለመወርቅ መታሰቢያ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ አባላቱን በማስተባበር ለወገን ጦር 695 ሺህ ብር የሚያወጡ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለጎንደር ከተማ አስተዳደር አስረክቧል፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት አቶ ኀይሉ ቀለመወርቅ የተደረገው ድጋፍ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ መታሰቢያ ማኅበሩ እስካሁን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ለኅልውና ዘመቻው ማበርከቱንም ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ የካዛንችስ አብሮ አደግ ጓደኛሞች ማኅበርም የተለያዩ የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ለኅልውና ዘመቻው እስካሁን በጎንደር ከተማ አስተዳደር 125 ሚሊዮን በጥሬ ገንዘብ እንደተሰበሰበና 120 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ነዋሪዎች መሰብሰብ መቻሉን ድጋፉን የተረከቡት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የህልውና ዘመቻው የስንቅ ዝግጅት አስተባባሪ አቶ ባዩ አቡሐይ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ምስጋናው ከፍያለው – ከጎንደር

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleበአማራ ክልል የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከ11 ቢሊዬን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
Next articleየፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ፡