
ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራ ልዑክ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ በአሸባሪው የህወሐት ቡድን የወደሙና ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች ተመልክቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ የትምህርት ቤቶቹ መሰረተ ልማቶች መውደሙን፣ የመማሪያ ፕላዝማዎች መዘረፋቸውን፣ ኮምፒውተርና የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስ ዘረፋና ውድመት እንደተፈጸመባቸው እና ትምህርት ቤቶችን በከባድ መሳሪያ መደብደባቸውን ተመልክቷል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማትን ከጎበኙ በኋላ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ትምህርት ቤቶችን ከመዝረፉ ባለፈ ድጋሚ አገልግሎት እንዳይሰጡ በማሰብ ማውደሙ የጨካኝነትና የክፋተኝነት ጥግ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ በሽብር ቡድኑ ዘረፋና ውድመት የተፈጸመባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
ትምህርት ቤቶቹን ደረጃቸውን ባሟላ መልኩ እንደገና መልሶ ለማቋቋም የፌዴራልና የክልል መንግሥት ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር ትምህርት ቤቶቹን እንደሚገነቡም ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማተብ ታፈረ ቡድኑ በአማራ ክልል ከአራት ሽህ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ውድመት ማድረሱን ገልጸዋል።
ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር መልሶ ግንባታዎች በአጭር ጊዜ እንደሚሠራም መግለጻቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
