የሽብር ቡድኑ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ ያደረሰው ውድመት የጭካኔ ገደብ የለሽነቱን ቢያሳይም የዓለም ጤና ድርጅት ዝምታ መምረጡን አምባሳደር ታየ አጽቀሥላሴ ገለጹ፡፡

255

ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች በወረራቸው አካባቢዎች ተቋማትን ዘርፏል፤ ያልቻለውን ደግሞ አውድሟል፡፡ አሸባሪው ቡድን የጥፋት ተልዕኮውን ከሚፈጽምባቸው ዋነኛው የጤና ተቋማት ይገኙበታል፡፡ የጤና አገልግሎት ተቋማቱ በመውደማቸውና በመዘረፋቸው በርካቶች ለህልፈተ ሕይወት እና ለጤና ችግር ተዳርገዋል፡፡ ይህንንም በተመለከተ የዓለም የጤና ድርጅት በጉዳዩ ዙሪያ ያለው ነገር የለም፡፡

የሽብር ቡድኑ ውድመትና ዘረፋ ካደረሰባቸው መካከል ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ይጠቀሳል፡፡

ይህንን አስመልክቶ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታየ አጽቀሥላሴ በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሑፍ እንዳሉት በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ የደረሰው ውድመት አሸባሪው ሕወሓት የጭካኔ ገደብ እንደሌለው በግልፅ ይመሰክራል። ይሄ ይቅር የማይባል ወንጀል ነው ብለዋል።

“የአሸባሪው ሕወሓት እኩይ ተግባራትን ብቻ ሳይኾን የዓለም ጤና ድርጅትን መስማት የተሳነው ዝምታ እናስታውሳለን” ነው ያሉት፡፡

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleየደቡብ ክልል በአፋር ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።
Next articleበአማራ ክልል የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከ11 ቢሊዬን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ