የደቡብ ክልል በአፋር ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

93

ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ክልል አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረገ።

የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ ድጋፉን ዛሬ በተረከቡበት ወቅት የደቡብ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ለተፈናቃዮች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን በዜጎች ላይ የፈጸመው ሰቆቃና ስቃይ እንዲሁም በሀገርና ሕዝብ ንብረት ላይ ያደረሰው ውድመት ከሰብዓዊ ፍጡር የማይጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያዊያን ቀፎው እንደተነካበት ንብ በአንድነት በመቆም የአሸባሪውን የጥፋት ሴራ ለመመከት እያደረጉት ያለው ተጋድሎ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ እየተደረገ ያለው ጥረት የሚያኮራ መሆኑን ጠቁመዋል። ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የደቡብ ክልል የመሠረተ-ልማት ክላስተር አስተባባሪና የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ በበኩላቸው ድጋፉ በመረዳዳትና በመተጋገዝ ባህል መሠረት ወገናዊ አጋርነትን ለማሳየትና የዜግነት ግዴታን ለመወጣት የተደረገ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

“የክልሉ መንግሥትና ሕዝብ ተጎጂዎች መልሰው እስኪቋቋሙ ድረስ የሚያደርጉት ድጋፉ ይቀጥላል” ብለዋል።

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous article❝ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ወቅታዊ ችግር በመፍታት የቀደመውን የፖለቲካና ማኅበራዊ ሁኔታ የማስቀጠል አቅም አላት❞ የኔፓል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባህራት ራጅ ፓውዲያል
Next articleየሽብር ቡድኑ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ ያደረሰው ውድመት የጭካኔ ገደብ የለሽነቱን ቢያሳይም የዓለም ጤና ድርጅት ዝምታ መምረጡን አምባሳደር ታየ አጽቀሥላሴ ገለጹ፡፡