
ታኅሣሥ 03/ 2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኔፓል የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ ከኔፓል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባህራት ራጅ ፓውዲያል ጋር ተወያይተዋል።
በወቅቱም አምባሳደር ትዝታ በኢትዮጵያ እና ኔፓል መካከል እ.ኤ.አ በ1971 የሁለትዮሽ ግንኙነት መመስረታቸውን አውስተዋል። ሀገራቱ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች በጋራ ጥቅሞቻቸው ዙሪያ በቅርበት እና በመተማመን መንፈስ የጋራ ትብብሮችን ሲያካሂዱ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ያጋጠሙ ችግሮችን በማስቆም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የወሰዳቸውን እርምጃዎች አብራርተዋል። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ደግሞ የሰላም አማራጭን ባለመቀበል በወረራቸው የአፋር እና አማራ ክልሎች ንጹሐንን መጨፍጨፉን ገልጸዋል።
አምባሳደሯ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት በመግለጽ ኔፓል በባለብዙ መድረኮች ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥልም ጠይቀዋል።
የኔፓል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባህራት ራጅ ፓውዲያል ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ወቅታዊ ችግር በመፍታት የቀደመውን የፖለቲካና ማኅበራዊ ሁኔታ የማስቀጠል አቅም እንዳላት ገልጸዋል።
የኔፓል መንግሥት በሁለትዮሽ እና የባለብዙ መድረኮች በጋራ ጥቅሞች ዙሪያ በትብብር ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት ሚኒስትሩ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
            
		