❝በሽብር ቡድኑ ዘረፋና ውድመት የተፈጸመባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለማቋቋም እየተሠራ ነው❞ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

124

ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራ ልዑክ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ምክንያት ዘረፋና ውድመት የተፈጸመባቸውን ትምህርት ቤቶች ተመልክቷል።

በሽብር ቡድኑ ውድመትና ዘረፋ የተፈጸመባቸው የኮኪት ሁለተኛ ደረጃ መሰናዶና የደብረዘቢጥ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤቶች የልዑካን ቡድኑ ከተመለከታቸው ውስጥ ይገኝበታል።

የልዑካን ቡድኑ የትምህርት ቤቶቹ መሰረተ ልማቶች መውደሙን፣ የመማሪያ ፕላዝማዎች መዘረፋቸውን፣ ኮምፒውተርና የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስ ዘረፋና ውድመት እንደተፈጸመባቸው መመልከቱን
ከመቄት ወረዳ ኮምዩኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

የሽብር ቡድኑ የተማሪዎችን ወንበሮች ለምግብ ማብሰያ ማገዶ በማድረግ እንደተጠቀመባቸው ተመልክቷል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደተናገሩት መግድል፣ መዝረፍና ማውደም የሽብር ቡድኑ መገለጫ ነው። በሽብር ቡድኑ የንብረት ዘረፋና ውድመት የተፈጸመባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለማቋቋም ትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous article❝አሸባሪው ቡድን ከፈጸመው የንብረት ውድመትና ዘረፋ ባለፈ ለእርዳታ የተዘጋጀን ቁሳቁስ በማውደም ለሀገር ያለውን ጥላቻ አሳይቷል❞ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከማል መሐመድ (ዶክተር)
Next article❝ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ወቅታዊ ችግር በመፍታት የቀደመውን የፖለቲካና ማኅበራዊ ሁኔታ የማስቀጠል አቅም አላት❞ የኔፓል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባህራት ራጅ ፓውዲያል