
ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከግል ተቋማት እስከ መንግሥት ሜጋ ፕሮጀክቶች ያካለለው የሽብር ቡድኑ ውድመት ከየፋብሪካዎቹ መግቢያ በር ጀምሮ እስከ ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ድረስ ውድመት ማድረሱን የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ከማል መሐመድ (ዶክተር) የሽብር ቡድኑ ከተማዋን በወረረበት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ማስከተሉን ገልጸዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ ባደረሰው ጉዳት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማት ቢሯቸው ተዘርፎና ሰነዶቻቸው መቃጠሉን ከንቲባው አመላክተዋል።
አሸባሪው ቡድን ከፈጸመው የንብረት ዘረፋና ውድመት ባለፈ ለእርዳታ የተዘጋጀን ቁሳቁስ በማውደም ለሀገር ያለውን ጥላቻ በተግባር አሳይቷል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ኤሊያስ ፈጠነ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
