የአማራ ባለሃብቶች ጥምረት ለሀገሩ ሕልውና ከልጁ ጋር በክብር ለተሰዋው አቶ እሸቴ ሞገስ ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡

202

አዲስ አበባ፡ ታኅሣሥ 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ባለሃብቶች ጥምረት ለሀገሩ ሕልውና ከልጁ ጋር በክብር ለተሰዋው አቶ እሸቴ ሞገስ ቤተሰቦች 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የተደረገውን ድጋፍ የባለሃብቶቹ ጥምረት ተወካይ አቶ ዮናስ መኮንን ለአቶ እሸቴ ሞገስ ታናሽ ወንድም ይተብቱ ሞገስ (ዶክተር) አስረክበዋል፡፡

የጀግናው ልጅ ሐና እሸቴ በአማራ ባለሐብቶች ጥምረት የተደረገላቸው ድጋፉ የቆየ የአንድነትና የመተሳሰብ እሴት አለመጥፋቱን ማረጋጫ መሆኑን ገልጻለች። “ለተደረገልን ውለታ ፈጣሪ ዋጋውን ይክፈላችሁ” በማለትም ምስጋና አቅርባለች።

ሌላኛዋ ልጃቸው ወርቅነሽ እሸቴ የአባታችን ቃል መከበሩ ደስ ብሎናል ነው ያለችው።

አቶ እሸቴ ሞገስ ከልጃቸው ይታገስ እሸቴ ጋር በመሆን በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘጠኝ አባላትን በጀግንነት በመግደል በክብር መሰዋታቸው ይታወሳል፡፡

ዘጋቢ፡-ድልነሳ መንግሥቴ-ከአዲስ አበባ

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq በዌብሳይት amharaweb.com በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleበጎንደር ከተማ አስተዳደር የሲቪክ ማኅበራት ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ አደረጉ፡፡
Next article“ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የአማራ ክልል ሕዝብ ኢንዱስትሪ አድርገን ነው የምናየው፤ ሁሉም የኔ ነው ብሎ ሊይዘው ይገባል” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)