
ጎንደር፡ ታሕሳስ 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር የሚገኙ 18 የሲቪክ ማኅበራት ለ180 ዘማች ቤተሰቦች ከ 1 ነጥብ 3 ሚልየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።
በርክክብ ሥነ – ሥርዓቱ ላይ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘዉዱ ማለደ የጎንደር ሕዝብ እና የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ሁልጊዜም ከዘማች ቤተሰቦች ጎን መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘዉዱ “አንድም የጀግና ቤተሰብ አያዝንም፣ አይተክዝም” ብለዋል።
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የገንዘብ ኢኮኖሚና ልማት ትብብር መምሪያ አስተባባሪ አበበ ካሴ የሲቪክ ማኅበራት ለ180 ዘማች ቤተሰቦች 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለዉ የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በከተማ አስተዳደሩ 27 መንግሥታዊ ያልሆኑ ፕሮጀክቶች አሉ ያሉት አቶ አበበ በቀጣይም ቀሪ ፕሮጀክቶች ሌሎች ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ነግረዉናል።
ድጋፍ የተደረገላቸዉ የዘማች ባለቤት ወይዘሮ ኤደን ብርሃኑ እና ወይዘሮ ፍሬሕይወት ፀጋዉ ለተደረገላቸዉ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ባለቤቶቻቸው ግንባር ቢዘምቱም እነሱም አካባቢያቸዉን ተደራጅተው እየጠበቁ እንደሆነ አስረድተዋል። ዘማች ባለቤቶቻቸውም አሸንፈው በድል እንደሚመለሱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡-አዲስ ዓለማየሁ – ከጎንደር
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq በዌብሳይት amharaweb.com በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation