ተጠርጣሪ ሰላይ መያዙን የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

187

ባሕር ዳር፡ መስከረም 23/2012 ዓ/ም (አብመድ) ከሁመራ ስልጠና ወስዶ ለስለላ ወደ መተማ የመጣ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ በኅብረተሰቡ ትብብር መያዙን የምዕራብ ጎንደር ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።

ተጠርጣሪው ከሌሎች 53 ግብረ አበሮቹ ጋር በጋራ በመሆን በሁመራ ስልጠና ሲወስድ መቆየቱን ቃሉን መስጠቱንም ነው የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዐባይ አሻግሬ የገለፁት።

ተጠርጣሪው ወንጀለኛ የስለላ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ መሆኑና ለጊዜው ያልተያዙ ሌሎች ሁለት ግብራ አበሮቹ መኖራቸውንም ነው ያስታወቁት።

ሌሎች ቀሪ 50 ሰዎች በነብስ ወከፍ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ታጥቀው የአካባቢውን ሠላም ለማወክ እንደገቡ እንደሚጠረጠርም ነው ዋና ኢንስፔክተሩ ያመለከቱት።

ኅብረተሰቡም ከፀጥታ አካሉ ጋር በጋራ ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር እያሳዬ ላለው ትብብርም አመሥግነዋል፡፡

ወቅቱ የእርሻ ሰብል የሚሰበሰብበት መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊው አርሶ አደሩ በሠላም ሰብሉን እንዳይሰበስብ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን እንዲታገልም ጥሪ አርበዋል።

ዘጋቢ፡- ዳንኤል ወርቄ

Previous articleየዚያ ዘመን ቅርሶች በዚህ ዘመን አይጠፉም!
Next article“የመገናኛ ብዙኃንን ጥፋት በዝምታ ማለፉ ተገቢ አይደለም።” አስተያዬት ሰጪዎች