ዓለም ዓቀፍ ገለልተኛ እና ለእውነት ቆመናል የሚሉ ተቋማት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የተፈጸሙ ወንጀሎችን ለዓለም እንዲያጋልጡ ጥሪ ቀረበ፡፡

117

ባሕርዳር፡ ታሕሳስ 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላያ ሠራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ከመፈጸም ባለፈ በአማራ እና አፋር ክልሎች ወረራ በማካሄድ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተለያዩ የጅምላ ጭፍጨፋ ፈጽሟል፡፡

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ በሽብር ቡድኑ በደልና ግፍ የደረሰባቸው ንጹሃን ዜጎች ፍትሕ እንዲያገኙ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በንጹሃን ዜጎች ላይ ያደረሰውን የጅምላ ግድያ ዓለም አቀፍ ተቋማት መመስከር መጀመራቸውን አስረድተዋል፡፡ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በፈጸማቸው የጀምላ ግድያዎች የሂውማን ራይትስወች ይፋ ባደረገው ሪፖርት በጭና እና በቆቦ በርካታ ንጹሃን ዜጎች በጅምላ መጨፍጨፋቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ ይህም የሽብር ቡድኑን ትክክለኛ ማንነት ያሳየ እንደነበር ነው የገለጹት፡፡

ዓለም ዓቀፍ ገለልተኛ እና ለእውነት ቆመናል የሚሉ ተቋማትም ሌሎች ይፋ ያልተደረጉና በሽብር ቡድኑ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ለዓለም እንዲያስረዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በዚህ ተግባር ለሚሰማሩም መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያመቻች ነው ያብራሩት፡፡

መንግሥት በአሸባሪ ቡድኑ የተፈጸሙ ወንጀሎችን በመመርመር እና ለንጹሃን ዜጎች ፍትሕ እንዲያገኙ እና ተጎጅዎችን ለመደገፍ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

በማኅበራ ዘርፍ ተማሪዎች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል የመሰብሰብ ሥራ መሥራታቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰብል ለመሰብሰብ የተቋረጠዉ ትምህርት ሰኞ እንደሚጀምርም ነው የተናገሩት። የባከነው ጊዜም እንደሚካካስ አስረድተዋል፡፡ ተማሪዎች የዘማቾችን ሰብል በመሰብሰብ፣ ደም በመለገስ፣ ስንቅ በማዘጋጀት እና ድጋፍ በማሰባሰብ በመሳተፋቸዉ መንግሥት ምስጋና ያቀርባልም ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀን አምባቸው

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq በዌብሳይት amharaweb.com በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleበጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የበቃ ዘመቻን በመቀላቀል ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ አስታወቁ
Next articleበአሽባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ቅድመዝግጅት መጠናቀቁን የአደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና እና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ገለጸ፡፡